የተሻሻለበት ጥር 12, 2021Person at work on a car wheel wearing a mask

በኮቪድ-19 ከተያዙ እና በቤት ውስጥ ለመቆየት የሐኪም ማስረጃ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ የእርስዎን ዶክተር፣ ክሊኒክ ወይም ምርመራ ያደረጉበትን ቦታ ማነጋገር ይችላሉ።

ለአሠሪዬ መታመሜን መንገር አለብኝ?

በምግብ ዝግጅት አገልግሎት ውስጥ የሚሠሩ ከሆነ፣ ኮቪድ-19 ተመርምረው ውጤትዎ ፖዘቲቭ መሆኑን ለቅርብ አለቃዎ መንገር እንዳለብዎት ሕጉ ያስገድዳል።

ማናቸውም ምርመራ ውጤቱ ፖዘቲቭ የሆነ እና በሥራ ቦታው ከሌሎች ሰዎች ጋር ቅርርብ ከነበረው፣ ማንኛውም ሰው ለአሠሪው ወይም ለቅርብ አለቃው ውጤቱን መናገር እንዳለበት አጥብቀን እንመክራለን።

የእኔ አሠሪ ለሥራ ባልደረባዎቼ ውጤቴ ፖዘቲቭ እንደሆነ ይነግራቸው ይሆን?

አሠሪዎች ሠራተኞቻቸው በሥራ ቦታቸው ላይ ለኮቪድ-19 ተጋልጠውየነበረ ከሆነ ይህንኑ እንዲናገሩ በሕግ ይገደዳሉ። በ አሜሪካ የአካል ጉዳት ሕግ (ADA) መሠረት የእርስዎን ስም ወይም መረጃ መግለጽ የለባቸውም።

የእኔ አሠሪ ስለ ኮቪድ-19 የበሽታ ምልክቶች እኔን ለምን ይጠይቀኛል?

በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ወቅት፣ አሠሪዎች ሠራተኞቻቸውን የበሽታ ምልክቶች የሚሰሟቸው መሆኑን መጠየቅ ይችላሉ። በ ADA መሠረት ሁሉን የሠራተኛ ሕመም እና ምስጢራዊ የሕክምና መዝገብ በምስጢር መያዝ አለባቸው።

የሥራ ቦታ ላይ ደኅንነት

በሥራ ቦታዎ ላይ ስላለ የጤና ስጋት ሪፖርት ለማድረግ Oregon OSHAን ያነጋግሩ። ወደ 503-229-5910 ይደውሉ ወይም ወደ osha.oregon.gov/workers ይሂዱ። 

ኮቪድ-19 ተመርምረው ውጤትዎ ፖዘቲቭ መሆኑን ለአሠሪዎ ስለነገሩ አግባብ ባልሆነ መንገድ እየታዩ እና እየተስተናገዱ እንደሆኑ ሆኖ ከተሰማዎት፣ Oregon Bureau of Labor and Industries (BOLI)ን ያነጋግሩ። ወደ 971-673-0761 ስልክ ይደውሉ ወይም ኢሜይል በዚህ አድራሻ ይላኩ፦ help@boli.state.or.us

የሕክምና ፈቃድ ማግኛ አማራጮች

  • የሚከፈልበት የሕመም ፈቃድ ጊዜ - የኦሪገን ሕግ የትርፍ ሰዓት ሠራተኞችን ጨምሮ ለሁሉም ሠራተኞች የሕመም ፈቃድ ይሰጣል። የእርስዎ አሠሪ 10 ወይም ከዚያ በላይ ሠራተኞች ካሉት ይህ መብት አልዎት (6 ወይም ከዚያ በላይ በፖርትላንድ ሲሆን)።
  • በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ለተፈጠረ ሥራ ፈትነት የሚሰጥ ድጋፍ - በኮቪድ-19 ምክንያት ሥራ የማይሠሩ ከሆነ እና ለመደበኛ ሥራ አጥነት መብት ብቁ ካልሆኑ፣ ለምሳሌ በራስ የሚተዳደር ወይም ሥራ ተቋራጭ ከሆኑ።
  • የኮቪድ-19 ጊዜያዊ የሚከፈልበት የዕረፍት መውጣት ፕሮግራም - በዶክተር ወይም በሕዝብ ጤና ጥበቃ በኩል ራስዎትን እንዲያገሉ ከታዘዙ፣ እና የእርስዎ አሠሪ የሚከፈልበት የዕረፍት ፈቃድን መስጠት የማይችል ከሆነ ወይም ሁሉንም የሕመም ፈቃድ ጊዜዎን የጨረሱ ከሆነ።