የተሻሻለው፦

10/4/2021

በ Oregon ውስጥ ያለ ማንኛውም ዕድሜው 12 እና ከዚያ በላይ የሆነ ሰው የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ይችላል። (ዕድሜያቸው ከ 12-17 ዓመት የሆኑት Pfizer ክትባትን ብቻ መከተብ ይችላሉ)  

እርስዎ የተከተቡ እንኳ ቢሆኑም፣ ለራስዎት እና ለቤተሰብዎ እንዲሁም ለጓደኞችዎ ጤና ጥንቃቄ ማድረጉን ይቀጥሉ። ሕመም ከተሰማዎት ቤት ይቆዩ፤ እጆችዎን ይታጠቡ፤ እና ቤተሰብ እና ጓደኞች ሕክምና እና የአእምሮ ጤና ድጋፍ እንዲያገኙ ያግዟቸው።

የኮቪድ-19 ክትባቶች ማኅበረሰቡን ከኮቪድ በሽታ እንዲጠበቅ ያደርጉታል

የኮቪድ-19 ክትባትን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

የኮቪድ-19 ክትባትን ማግኘት የሚቻልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፦

 • Multnomah County በመደበኛነት ከማክሰኞ እስከ ቅዳሜ የኮቪድ-19 ክትባት መስጫ ክሊኒኮችን አዘጋጅቶ አገልግሎት ይሰጣል። የ Multco Weekly Clinics ዘንድ ይሂዱ ወይም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ 503.988.8939 ይደውሉ።

ክትባት በሚከተቡበት ወቅት ምን ሊያጋጥመኝ ይችላል ብለው መጠበቅ ይችላሉ

 • የአሜሪካ ዜጋ የግድ መሆን የለብዎትም። 

 • ክትባት መከተብ በእርስዎ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ሂደት ላይ ጫና አይፈጥርም ወይም እንደ የሕግ ጥሰት አይቆጠርም። 

 • የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥር ሊኖርዎት ወይም ቊጥሩን መስጠት አያስፈልግዎትም። 

 • የጤና የመድኅን ዋስትና እንዲኖርዎት አያስፈልግም።

 • ክትባቱ የሚሰጠው በነጻ ነው።

ወደ ክትባት ቀጠሮዎ ለመሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት ይፈልጋሉ? ወደ 211 ወይም 1-866-698-6155 ይደውሉ።

ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሕፃናት የሚሰጡ ክትባቶች

 • ዕድሜያቸው ከ 15-17 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች አብሯቸው የሚመጣ ዐዋቂ ሰው አያስፈልጋቸውም፣ እና በኦሬጎን ̈Oregon ግዛት ውስጥ ለመከተብ የወላጅ ፈቃድ ማግኘት አይጠበቅባቸውም። ወጣቶች ሕክምናን በተመለከተ ከውሳኔ ላይ ሲደርሱ የሚያምኗቸውን ዓዋቂ ሰዎች በጉዳዩ ላይ እንዲሳተፉበት እንዲያደርጉ እናበረታታለን። 

 • ዕድሜያቸው ከ 12-14 ዓመት የሆኑ ሕፃናት አብሯቸው የሚመጣ ወላጅ፣ አሳዳጊ ሞግዚት ወይም ሌላ ከእነርሱ ጋር እንዲሆን በወላጅ ሥልጣን የተሰጠው ሰው አብሯቸው ሊኖር ያስፈልጋቸዋል።

 • ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ ሞግዚት ውጭ ሌላ ሰው ዕድሜያቸው ከ12-14 ዓመት ከሆኑ ሕፃናት ጋር አብሮ ከመጣ፣ ከወላጅ/አሳዳጊ ሞግዚት ፈቃድ ማግኘታቸውን ማረጋገጫ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው። ለአንዳንድ ሕክምና ነክ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ወላጅ ወይም አሳዳጊ ሞግዚት በስልክ ጥሪ የሚገኙ መሆን አለባቸው። የፈቃድ ማረጋገጫ ከእነዚህ በአንዱ መቅረብ ይችላል፦

  • የተፈረመ የፈቃድ መስጫ ቅጽ፣ ወይም

  • የወላጅ/አሳዳጊ ሞግዚት ስም፣ ከታዳጊው ጋር ያላቸው ዝምድና፣ የታዳጊው ልደት ቀን፣ ወላጅ/አሳዳጊ ሞግዚት ታዳጊው እንዲከተብ ፈቃደኛ መሆኑን የሚገልጽ በጽሑፍ የተጠቀሰ ቃል፣ እና የወላጅ/አሳዳጊ ሞግዚት ፊርማ የሚያካትት በእጅ ጽሑፍ ወይም በታይፕ የተዘጋጀ ማስታወሻ።

ከዚህ በተጨማሪ እንዲህ ማድረግ ይችላሉ፦

ተጨማሪ የኮቪድ-19 ክትባት መረጃ ምንጮች

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ እና ሕዝብ ከሚሰበስብባቸው ቦታዎች መራቅ

የ Oregon ግዛት አብዛኛዎቹን የኮቪድ-19 ገደቦችን አንሥቷል። የአፍና አፍንጭ መሸፈኛ ጭንብሎች እና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በአብዛኛዎች የሥራ ቦታዎች ላይ አስፈላጊ አይደሉም። ግለሰቦች እን ቡድኖች ማናቸውም ብዛት ያላቸውን ስብሰባዎችን ማድረግ ይችላሉ። 

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች እና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አሁንም በሚከተሉት ቦታዎች ላይ ያስፈልጋሉ፦

 • አይሮፕላን ማረፊያዎች እና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች

 • የዐዋቂ ሰዎች እና የወጣቶች ማረሚያ ቤቶች

 • የጤና እንክብካቤ መስጫ ተቋማት

 • መጠለያዎች እና ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ

Multnomah County የኅብረተሰብ ጤና አማካሪ አካል፦ ሙሉ በሙሉ ካልተከተቡ፣ በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ማድረግዎን እንዲቀጥሉ እና አካላዊ ርቀትዎን እንዲጠብቁ እንመክርዎታለን፦

 • ሙሉ በሙሉ ካልተከተቡ ከእርስዎ ጋር ከማይኖሩ ሰዎች ጋር በአንድ ቤት አብረው በሚሆኑበት ጊዜ እና

 • ሕዝብ በሚሰበስብበት ክፍል ውስጥ ሲሆኑ ወይም አጠገብዎ ያለ ሰው መከተብ አለመከተቡን በማያውቁበት ጊዜ

ሙሉ በሙሉ መከተብ ማለት Pfizer ወይም Moderna 2ኛ ክትባት ከወሰዱ 2 ሳምንት ከሆንዎት ወይም Johnson & Johnson ክትባት ከተከተቡ 2 ሳምንት ከሞላዎት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ የ Oregon የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የተመለከተ መረጃ

የኮቪድ-19 ስርጭትን ይከላከሉ 

ኮቪድ-19ን የሚያመጣው ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ መተላለፍ ይችላል። በበሽታው ላለመያዝ፡

 • ቢያንስ ለ20 ሰከንድ እጆችዎን ደጋግመው ይታጠቡ

 • ከቤት ሲወጡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያድርጉ

 • ፊትዎን በእጅዎ መንካትን ያስወግዱ

 • ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ አፍዎን ይሸፍኑ

 • አብረው ከማይኖሩዋቸው ሰዎች ቢያንስ 6 ጫማ ያክል ርቀት ይጠብቁ

 • ስብሰባዎችን አነስተኛ ብዛት ያለው ሰው የሚገኝባቸው፣ ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ እና በተቻለ መጠን ከቤት ውጭ እንዲደረጉ ያድርጓቸው

 • በተደጋጋሚ በእጅ የሚነኩ ነገሮችን በአልኮል ያጽዷቸው

 • ጉዞዎችን ይገድቡ እና ከቤትዎ አቅራቢያ ይቆዩ

 • ይከተቡ

እንደ አስም፣ ስኳር በሽታ፣ የልብ ወይም ሳንባ በሽታ የመሳሰሉ ተጓዳኝ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በኮቪድ-19 በከፍተኛ ደረጃ መታመም የመቻላቸው ስጋት በጣም ከፍተኛ ነው። ከበርካታ ሰዎች ጋር የሚኖሩ ከሆኑ እንዴት ደኅንነትዎን መጠበቅ እንደሚችሉ የተሰጡትን ጠቃሚ ምክሮች ይመልከቱ።

ሕመም ከተሰማዎት

የሕመም ስሜት ሊስማዎት ከጀመረ - በተለይ ትኩሳት እና ሳል ካለብዎት፡

 • በቤት ይቆዩ እና ከሌሎች ሰዎች ይራቁ። 

 • ምርመራ ማድረግ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ወደ ሃኪምዎ ወይም ክሊኒክዎ ይደውሉ።

 • የእርስዎን ሃኪም ወይም ክሊኒክ ከሌሎች ሰዎች ጋር መቀላቀል ይችላሉ ብሎ እስከሚነግርዎት ድረስ በቤት ውስጥ ይቆዩ።

 • የተሻለ ስሜት እንዲሰማዎት በተለምዶ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ማድረግ ይቀጥሉ፦ ይተኙ፣ ዕረፍት ያድርጉ እና ብዙ ፈሳሽ ይጠጡ።

 • ለኮቪድ-19 ልዩ መድሃኒት የለውም።  

ከእነዚህ ድንገተኛ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች መካከል እርስዎ ወይም በሌላ በማናቸውም ዕድሜ ላይ ያለ ሰው ከታየባችሁ ወዲያውኑ ድንገተኛ የሕክምና እርዳታውን ወዲያውኑ ለማግኘት ሞክሩ፦

 • ለመተንፈስ መቸገር

 • የማያቋርጥ ሕመም ወይም ደረት ላይ የሚሰማ ውጋት

 • አዲስ ግራ የመጋባት ስሜት

 • ለመንቃት ወይም እንደነቁ ለመቆየት መቸገር

 • የከንፈር ወይም የፊት ሰማያዊ መሆን

 • ከባድ የሆድ ቁርጠት

 • ወደ 911 ወይም ወደ በእርስዎ አካባቢ የሚገኝ የድንገተኛ ሕክምና መስጫ ተቋም ጋር ይደውሉ።

 • ለኦፐሬተሩ/ዋ እርስዎ ወይም እርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ኮቪድ-19 ተይዛችሁ ሊሆን እንደሚችል ይንገሩት/ዋት።

ለራስዎ ጤንነት ጥንቃቄ ለማድረግ በቤት ውስጥ የመተንፈሻ አካል የበሽታ ምልክቶችን መቆጣጠር የሚያስችሉ 10 መንገዶች የሚለውን ይመልከቱ

የኮቪድ-19 ምርመራ

የኮቪድ-19 የበሽታ ምልክቶች ካሉብዎት ወይም ኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ከነበርዎት መመርመር አለብዎት። የቅርብ ንክኪ ማለት በአንድ ቀን ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አድርገውም ሆነ ሳያደርጉ ከሌላ ሰው ጋር ለ15 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ በስድስት ጫማ ርቀት ውስጥ አብሮ መቆየት ማለት ነው።

 • የምርመራ ውጤትዎን እስከሚያገኙ ድረስ በቤት ውስጥ መቆየት እና ከሌሎች ሰዎች ራስዎን ማራቅ ይኖርብዎታል።

 • የኮቪድ-19 ምርመራን የት እና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ “የት መመርመር እችላለሁ?” የሚለውን ይመልከቱ 

ከተመረመሩ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብዎት።

ለእርስዎ ቤተሰብ ጥንቃቄ ማድረግ

የግል ሃኪም ከሌልዎት፣ ወደ 211 ወይም ወደ Multnomah County Primary Care Health Centers በስልክ ቁጥር 503-988-5558 ይደውሉ። አስተርጓሚዎችን ማግኘት ይችላል። በ Multnomah County ክሊኒክ

 • የጤና መድን ዋስትና እንዲኖርዎት አይገደዱም።

 • ገቢ እንዲኖርዎት አይገደዱም።

 • የኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ምንም ሆነ ምን፣ የጤና እንክብካቤ ማግኘት ይችላሉ።

 • የእርስዎን መረጃ ለሕግ አስከባሪዎች ወይም ለኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት አሳልፈን አንሰጥም።

የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ሕግ አስከባሪ በሆስፒታሎች፣ በሃኪም ቢሮዎች፣ በጤና ጣቢያዎች እና በድንገተኛ ወይም አጣዳፊ የሕክምና መስጫ ተቋማት ውስጥ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋልን የሚከለክል ፖሊሲ አለው። 

ለኮቪድ-19 የሕክምና እርዳታ ወይም አገልግሎቶችን ካገኙ፣ እርስዎ በአሜሪካ የቋሚነት መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በሚያመለክቱበት ጊዜ በእርስዎ ላይ ይህ ጉዳይ ምንም ችግር አያመጣብዎትም። ስለ ሕግ ጥሰት ክስ ተጨማሪ ያንብቡ።

ምንጮች

ስለ ኮሮና ቫይረስ፣ እንዴት እንሚተላለፍ እና እንዴት ጤናማ እንደሆኑ መቆየት እንደሚችሉ አጠቃላይ መረጃ

ጥያቄዎች?

211 መረጃ ን ይጎብኙ ወይም ወደ 2-1-1 ከጠዋቱ 8 am እስከ ቀኑ 11 pm ድረስ ይደውሉ። የትርጉም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።