የተሻሻለበት 2/15/2022

ለራስዎ ተጨማሪ እንክብካቤ ያድርጉ እንዲሁም በዚህ ከባድ ጊዜ ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ።  አንዳንድ ቀን ደህና ስሜት ሊሰማዎት ሆኖም ግን በሚቀጥለው ቀን ሊጨነቁ፣ ሊፈሩ ወይም ሊበሳጩ ይችላሉ።  ይህ ጤናማ ሁኔታ ነው።

የራስዎን የአእምሮ እና አካላዊ ጤና ለመጠበቅ በየቀኑ ሊያደርጓቸው የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።

የአእምሮ ጤንነት

 • ላፍታ አረፍ ይበሉ እና በጥልቀት ደጋግመው ይተንፍሱ።
 • ለራስዎ ቀና ይሁኑ።
 • ከስክሪኖች በመደበኛነት ዕረፍት ይውሰዱ።
 • ሲያስፈልግ ለብቻዎ ሆነው ጊዜዎን ያሳልፉ።
 • ከጓደኞች፣ ከማኅበረሰብ እና ከእምነት ተቋማት ጋር ያልዎትን ግንኙነት ኦንላይን ያድርጉ።
 • በተፈጥሮ ይዝናኑ።
 • መቆጣጠር የሚችሉትን እና የማይችሉትን ለይተው ይወቁ።

አካላዊ ጤና

 • መደበኛ መርሐ ግብር ይኑርዎት።
 • ሰዓትዎን ጠብቀው ይመገቡ እና ቀኑን በሙሉ ውሃ ደጋግመው ይጠጡ።
 • ሰውነትዎን ያንቀሳቅሱ።
 • በቂ እንቅልፍ ለማግኘት እና ዕረፍት ለማድረግ የሚያስችልዎትን ጊዜ ለማግኘት ይሞክሩ።

የአእምሮ እና የስሜታዊ ድጋፍ ከፈለጉ ወደ አስተማማኝ + ጠንካራ የእርዳታመስመር 800-923-4357 መደወል ይችላሉ