drive-up COVID-19 testing at East County Health Center

9/15/2021

የኮቪድ-19 ምርመራ

እርስዎ የኮቪድ-19 የበሽታ ምልክቶችካሉብዎት ወይም በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ከነበርዎት መመርመር አለብዎት። የቅርብ ንክኪማለት በአንድ ቀን ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሽፈኛ ጭንብል አድርገውም ሆነ ሳያደርጉ ከሆነ ከሌላ ሰው ጋር ለ15 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ በ6 ጫማ ርቀት ውስጥ አብሮ መቆየት ማለት ነው።

በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ስለነበርዎት እየተመረመሩ ከሆነ፣ ምርመራውን ከማድረግዎ በፊት ቢያንስ ከንክኪው 4 ቀናት በኋላ ቢመረመሩ በጣም የተሻለ ነው። ቶሎ ከተመረመሩ ምርመራው ውጤት ላያስገኝ ይችላል። በቤትዎ ውስጥ መቆየት እና ራስዎን ከሌሎች ሰዎች ማራቅ ይኖርብዎታል።

በእርስዎ ሐኪም ቢሮ ወይም ክሊኒክ ውስጥ መመርመር ይችላሉ። የራስዎ ሐኪም ከሌልዎት፣ ህዝብ የምርመራ ጣቢያ ውስጥ መመርመር ይችላሉ። 

የማኅበረሰብ ምርመራ ጣቢያዎች

ለማናቸውም የበሽታ ምልክቶች ላሉበት ወይም በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ለነበረው ለማናቸውም ሰው ያለ ምንም ወጪ ነጻ ምርመራ በቀጠሮ ማግኘት ይችላል። 

ለቀጠሮ ወይም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ 503-988-8939 ይደውሉ። አስተርጓሚዎችን ማግኘት ይችላል።

የምርመራ ጣቢያ ቦታዎች እና የስራ ሰዓታት

የምርመራ ቦታ የስራ ሰዓት ወይም ቦታ ሊለወጥ ይችላል፤ ደግሞም አዳዲስ ጣቢያዎች ሊጨመሩ ይችላሉ። ለተሻሻለው መረጃ ይደውሉ።

Fabric Depot
700 SE 122nd Ave., Portland [map]
ማክሰኞ, 8:30 am to 3:45pm 

Mid County Community Testing - IRCO
10301 NE Glisan St, Portland
ዓርብ- 11:00 a.m. to 1:30 p.m.

Rockwood Community Testing - Latino Network
312 SE 165th Ave. Portland
 ቅዳሜ -ከ 9:00 እስከ11:00 a.m. ጠዋቱ

ምርመራ፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታ እና የሕዝብ ኃላፊነት 

  • በእኛ የማኅበረሰብ ጣቢያዎች ለመመርመር የሙልትኖማህ ካውንቲ ነዋሪ መሆን ወይም የጤና መድን ዋስትና መኖር አያስፈልግዎትም።

  • የኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ምንም ሆነ ምን መመርመር ይችላሉ። 

  • የእርስዎን መረጃ ለሕግ አስከባሪዎች ወይም ለኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት አሳልፈን አንሰጥም።

የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ሕግ አስከባሪ አካል እንደ ሆስፒታል፣ የዶክተር ቢሮዎች፣ የጤና አገልግሎት መስጫ ክሊኒኮች፣ እና ድንገተኛ ወይም አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ መስጫ ተቋማት ውስጥ ተጠርጣሪን ያለመያዝ ፖሊሲ አለው።

ለኮቪድ-19 የሕክምና እርዳታ ወይም አገልግሎቶችን ካገኙ፣ እርስዎ በአሜሪካ የቋሚነት መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በሚያመለክቱበት ጊዜ በእርስዎ ላይ ይህ ጉዳይ ምንም ችግር አያመጣብዎትም። ስለ የሕዝብ ኃላፊነት ተጨማሪ ያንብቡ።

OHSU ምርመራ ማዕከል

ወደ 833-647-8222 ይደውሉ ወይም የOHSU የድር ጣቢያ ትክክለኛ ቦታዎችን እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይጎብኙ።

ከተመረመሩ በኋላ

ውጤትዎ ፖዘቲቭ ከሆነ

እርምጃ 1፡ በቤት ውስጥ ይቆዩ እና አብረዋቸው ከሚኖሩ ሰዎች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ራስዎን ያርቁ። እርስዎ የበሽታ ምልክቶች ካልዎት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብረው መሆን የሚችሉት፡

  • መድኃኒት ሳይጠቀሙ ለ24 ሰዓታት ምንም ትኩሳት ካልነበረብዎት፣ እና
  • የበሽታው ምልክቶች (ስሜቶች) የተሻልዎት ከሆነ፣ እና
  • የበሽታ ምልክቶቹ ካቆሙ ቢያንስ 10 ቀናት ያለፍዎት ከሆነ

እርስዎ የበሽታ ምልክቶችከሌልዎት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብረው መሆን የሚችሉት፦

  • ምርመራ ካደረጉ 10 ቀናት ካለፉ እና ምንም የበሽታ ምልክቶች ከሌልዎት

ከእርስዎ ጋር የሚኖሩ ሰዎችም በቤት ውስጥ መቆየት እና ከእርስዎ ቤተሰብ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለ14 ቀናት ማቆም አለባቸው። ስለ እነዚህ ነገሮች ጥያቄዎች ካልዎት፣ ወደ እርስዎ ዶክተር ስልክ ይደውሉ።

እርምጃ 2፡ ከእርስዎ ጋር የቅርብ ንክኪ ላላቸው ሰዎች በሙሉ እርስዎ ተመርምረው ውጤትዎ ፖዘቲቭ እንደሆነ ይንገሯቸው። “የቅርብ ንክኪ” ማለት በአንድ ቀን ውስጥ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አድርገውም ሆነ ሳያደርጉ ለ15 ደቂቃ አብረዋቸው የቆዩት ሰው ማለት ነው። ከእርስዎ አጠገብ ለመጨረሻ ጊዜ አብረው ከነበሩበት ቀን ጀምሮ ለ14 ቀናት በቤት ውስጥ መቆየት እና ምንም እንኳ የበሽታ ምልክቶች ባይኖሩባቸውም የኮቪድ-19 ምርመራን ማድረግ እንዳለባቸው ይንገሯቸው

  • እርስዎ የበሽታ ምልክቶች ካሉብዎት፦ የእርስዎ የበሽታ ምልክቶች መታየት ከጀመሩባቸው 2 ቀናት በፊት ከእርስዎ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ሁኔታውን ያሳውቋቸው።
  • እርስዎ የበሽታ ምልክቶች ከሌሉብዎት፡ የእርስዎን የኮቪድ-19 ምርመራ ከማድረግዎ በፊት ካሉት 2 ቀናት ጀምሮ ከእርስዎ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ሁኔታውን ያሳውቋቸው። 

እርምጃ 3፡ ሲያስፈልግዎት እገዛ ያግኙ። ራስዎትን ለማግለል ወይም ኳራንታይን ለማድረግ እገዛ ካስፈለግዎት ወደ 2-1-1 ይደውሉ። ለእርስዎ የሚያስፈልግዎትን ግብዓቶች በማቅረብ ሊያግዝዎት ይችላሉ (ምግቦች፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የቤት ኪራይ ድጋፍ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች)። 

የሕዝብ ጤና ጥበቃ ሠራተኛ ለእርስዎ ስልክ ሊደውልልዎት ይችላል። ከእርስዎ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ማግኘትና ማናገር ላይ እገዛ ካስፈለግዎት እገዛ ሊያደርግልዎት ይችላሉ። እባክዎ ሲደውልልዎት መልስ ይስጡዋቸው። የእርስዎን መረጃ ለሕግ አስከባሪዎች ወይም ለኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት አሳልፈው አይሰጡም።

የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤትዎ ኔጋቲቭ ከሆነ

በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ከነበርዎት ከእነርሱ ጋር ከነበሩበት ቀን ጀምሮ ለ 14 ቀናት በቤት ውስጥ ራስዎን ከሰው አርቀው ያቆዩ--ይህ ኳራንታይን ይባላል። በቤት ውስጥ መቆየት እና ራስን ከሌሎች ከእርስዎ ጋር ከማይኖሩ ሰዎች ለ14 ቀናት ማራቅ የኮቪድ-19ን ወደ ሌሎች የሚኖረውን ስርጭት ለመከላከል ለደኅንነት አስተማማኙ መንገድ ነው።

ምንም የበሽታ ምልክቶች ከሌሉብዎት፣ እና ብዙ ሰው ባለበት ቦታ የማይሠሩ ወይም ጊዜ የማያሳልፉ ከሆነ -- ለምሳሌ ያሉበት ቦታ ለረዥም ጊዜ ሕክምና በሚሰጥበት ቦታ ላይ ከሆነ -- ኳራንታይኑን ከ10 ቀናት በኋላ ማቆም ይችላሉ። ከባድ ለሆነ በሽታ የመጋለጥ ዕድል ካለው ሰው ጋር አብረው የሚኖሩ ከሆነ፣ 14ቱን ቀን በሙሉ ኳራንታይን ይኖርብዎታል። ማናቸውም የበሽታ ምልክቶች ከታየብዎት ወደ የእርስዎ ዶክተር ስልክ ይደውሉ።

ራስዎትን እና ሌሎችን ከበሽታው መጠበቅዎን ይቀጥሉ፡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያድርጉ፣ 6 ጫማ ርቀት ይጠብቁ፣ እጅዎን ደጋግመው በሳሙና ይታጠቡ።