የዘመነው በነሐሴ 5/19/2022

ጭምብሎች እና ክትባቶች ማህበረሰባችንን ከCOVID-19 ለመጠበቅ ከሚደረጉ ደረጃዊ አካሄዶች ውስጥ አንዱ ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ የጭምብል ማድረግ ግዴታ መጋቢት 12 ቀን 2022 ዓ.ም. የተነሳ ቢሆንም፣ ለአብዛኛው ውጪ የህዝብ ቦታዎች ጭምብሎች የCOVID-19 ስርጭት ለመቀንስ አስፈላጊ የህዝብ ጤና መሳሪያ ነው።

እድሜያቸው ከ 2 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ወይም የለበሱትን በራሳቸው ማውለቅ የማይችሉ ሰዎች የፊት መሸፈኛዎችን ማድረግ የለባቸውም።

የተወሰኑ አካባቢዎች ጭብል ማድረግ ይጠይቃሉ፥

  • እንደ ሆስፒታሎች፣ የረጅም ጊዜ እንክብካቤ ተቋማት፣ ክሊኒኮች እና የሐኪሞች ቢሮዎች ያሉ የጤና እንክብካቤ ቅንብሮች
  • የዐዋቂ ሰዎች እና የወጣቶች ማረሚያ ቤቶች
  • መጠለያዎች እና ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ

አውቶብሶችን፣ MAXን እና በአየር የሚደረጉ ጉዞዎችን ጨምሮ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎች ላይ፣

  • የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆነ ወይም ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋ ለሚኖሩ ሰዎች በጥብቅ ይመከራል።
  • ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ጨምሮ ክትባት ያልወሰዱ ሰዎችን ከበሽታ ለመጠበቅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሁሉም ሰው እንዲያደርግ ይመከራል።

COVID-19 ካለብዎት፣ ቢያንስ ለ5 ቀናት ራስዎን ማግለል (ከሌሎች ማራቅ)፣ እና በሌሎች አካባቢ ቢያንስ ለ 5 ቀናት ጭምብል ማድረግ አለብዎት። ለይቶ ማቆያ እና ራስን ማግለልመመሪያዎችን ይከተሉ

ትምህርት ቤቶች፣ ድርጅቶች፣ እና አካባቢያዊ የንግድ ስራዎች የጭምብል ግዴታን መቀጠል ይችላሉ። ይዘጋጁ። በሚወጡበት ጊዜ ለማንኛውም ጭምብል ይዘው ይንቀሳቀሱ!

ጭምብል መምረጥ

የፊት መሸፈኛዎች በብዙ መልኩ ይመጣሉ። ከታማኝ ምንጭ N95፣ KN95 እና KF94 መተንፈሻ ለመግዛት ያስቡ። ሆኖም፣ አንዴ ተጠቅመው የሚጥሏቸው የቀዶ ጥገና ጭምብሎች ወይም የጨርቅ ጭምብሎች ያሉ ሌሎች አማራጮች አሉ። 

ጭምብል ሲመርጡ እና ሲለብሱ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ሁለት በጣም አስፈላጊ ነገሮች፦

  • የእርስዎን የአተነፋፈስ ጠብታዎችዎን ወደ ውስጥ እና የሌሎች በውጭ የሚያስቀሩ ብዙ ንብርብሮች ያላቸውን ጭምብሎች ይምረጡ። ተደራራቢ ሽፋን ያለው ጭንብል ተጨማሪ የመተንፈሻ ጠብታዎች ወደ ጭንብልዎ ውስጥ መግባታቸውን ወይም ከታመሙ ከጭንብልዎ እንዳያመልጡ ያቆማል። በቀዶ ሕክምና ጭምብል ላይ የጨርቅ ጭንብል ማድረግ ይችላሉ። 
  • ጭንብልዎ ከፊትዎ ጋር በትክክል እንደገጠመ ያረጋግጡ። ክፍተቶች በመተንፈሻ ጠብታዎች ውስጥ አየር ወደ ውስጥ እና ወደ ውጪ በጭምብሉ ጠርዝ አካባቢ እንዲያልፉ ሊያደርግ ይችላል።

መድልዎ ህጉን የሚጣረስ ነው

ጥሰት እና ማግለል በጥቁሮች፣ በተወላጆች እና በቀለም ማህበረሰቦች ህዝቦች ላይ በየቀኑ የሚደርስ ክስተት ሆኗል። ጭምብል ለሚለብሱ ጥቁር፣ ተወላጆች እና የቀለም ሰዎች ላይ የሚሰነዘሩ ዘረኝነት እና የዘረኝነት ምላሾች አሁን ባለንበት ሁኔታ ያለ እውነት ነው። እና ሆኖም ጭምብሎች ጤናማ ሆነ ለመቆየት እና ነፍስ ለመታደግ ሊረዱ እንደሚችሉ እናውቃለን። Multnomah County ሰዎች ላይ በዘራቸው፣ በብሄራቸው፣ ወይም ማንነታቸው የተነሳ ጥቃት ማድረስን ወይም መድልዎን አይታገስም

ይለግሱ

 Multnomah County የጨርቅ መሸፈኛዎች እና የህክምና ጭምብሎች ልገሳዎችን እየተቀበለ ይገኛል