gramma and grandaughter together washing hands 2/15/2022

የመኖሪያ ቦታ የሚጋሩ ከሆነ ጠቃሚ ምክሮች

ብዙዎቻችን ከብዙ ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት አጋሮች ጋር በአንድ ቤት ውስጥ፣ አልያም ከልጆች፣ ከአያቶች እና ወላጆች ጋር እንኖራለን።

ከ 65 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ሰዎች፣ ወይም ህክምና ክትትል እየተደረገበት የሳንባ በሽታ፣ የልብ በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ አስም፣ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከCOVID-19 በጣም የመታመም ተጋላጭነታቸው ከፍ ነው። ቤት ውስጥ ያለ አንድ ሰው ተጋላጭ ከሆነ፣ እነሱን ለመጠበቅ ሁሉም ሰው በበሽታው ላለመያዝ በጣም መጠንቀቅ አለበት።

አብረን፣ ጤናማ ሆነን መኖር እንዴት እንደምንችል አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች አሉ።

መከተብ እና/ወይም ማጠናከሪያ ይውሰዱ

ዕድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉም ሰዎች ለኮቪድ-19 መከተብ ይችላሉ። እራስዎን እና ሌሎችን ለመጠበቅ መከተብ በጣም አስፈላጊ ነው። ክትባቶች ከከባድ ሕመም እና ሞት ለመታደግ ጥሩ መከላከያ ይሰጣሉ።

የማጠናከሪያ ክትባት ለሁሉም የተከተቡ አዋቂዎች ረጅም ዘላቂ ጥበቃ ለማግኘት የሚመከር ተጨማሪ ክትባት ነው። ብዙ ክትባቶች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ማጠናከሪያዎች ያስፈልጋቸዋል። የማጠናከሪያ ውስዶች እርስዎን እንደ Omicron ካሉ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ለመጠበቅ ያግዙዎታል።

በየቀኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች

ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች ያህል እጆችን በተደጋጋሚ በሳሙና እና ውሃ ይታጠቡ።

 • ወደ ቤት ሲመለሱ፣ ከመመገብዎ በፊት፣ ጽዳት ካፀዱ በኋላ፣ እና መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ መታጠብዎን ያረጋግጡ።

 • ቤተሰቦች እጆችን ሲታጠቡ የ20-ሴኮንድ መዝሙር አብረው በመዘመር እጅ መታጠብን ወደ ጨዋታ መቀየር ይችላሉ።

ባልታጠቡ እጆች አይንዎን፣ አፍንጫዎን፣ ወይም አፍዎን አይንኩ።

ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ሶፍት ይጠቀሙ፤ ወይም የክርንዎን ውስጣዊ ክፍል ይጠቀሙ። የተጠቀሙበትን ሶፍት ይጣሉና ቀጥለው እጅዎን ይታጠቡ።

ብዙ ጊዜ የሚነካኩትን እንደ ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የበር መያዣዎች፣ መብራት ማብሪያ እና ማጥፊያዎች፣ ሪሞቶች፣ አሻንጉሊቶች፣ ሽንት ቤቶች፣ እና ገንዳዎች ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ያፅዱ እና ከጀርም ነፃ ያድርጉ። ሲቻል፣ የሚጣሉ ጓንቶችን ይጠቀሙ እና/ወይም ስፍራዎችን ካፀዱ በኋላ እጆችን ይታጠቡ።

young men making dinner togetherለሁሉም ሰው ጤና ያቅዱ

 • ከታመሙ እንዴት እንክብካቤ እንደሚያኙ እቅድ ያውጡ። ለቤተሰብዎ እቅድዎን ያጋሩ። የሐኪምዎን ወይም የክሊኒክዎን ስም እና ስልክ ቁጥር ያካቱ። ቀጣይነት ያላቸው የጤና ችግሮችን ማለትም እንደ አስም ወይም የስኳር በሽታ እና ለዚህግ የግድ መወሰድ ያለባቸውን መድኃኒቶችን የተመለከተ መረጃን ያካቱ።

 • ልጆችዎን ወይም ቤትዎ ውስጥ ያሉ ክትትል ወይም እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሌሎች ሰዎችን ማን እንደሚንከባከባቸው እቅድ ያውጡ።

 • ለከፋ ህመም ከፍ ያለ አደጋ ላይ የሚጥልዎ ቀጣይ የጤና እክሎች (የታወቁ ችግሮች) ካለብዎ፣ ለጥቂት ሳምንታት ቤት ውስጥ መቆየት ሊኖርብዎት ስለሚችሉ በቂ መድሃኒቶች እና አቅርቦቶች አንዳልዎት ያረጋግጡ።

አንድ ሰው ካመመው

 • ለዚያ ሰው ለማረፍያ እና ለማገገምያ የተለየ ቦታ ለማዘጋጀት ይሞክሩ።

 • ከተቻለ፣ ለታመመው ሰው የራሱ መፀዳጃ ቤት ያዘጋጁለት።

 • አንድ መፀዳጃ ቤት ብቻ ካለ፣ የታመመው ሰው ከተጠቀመው በኋላ መፀዳቱን ያረጋግጡ።

 • ፎጣዎችን፣ አልጋን፣ ምግብን፣ የፊት መሸፈኛዎችን ወይም መመገቢያ ዕቃዎችን አይጋሩ።

 • የታመመውን ሰው እንዲንከባከብ ቤቱ ውስጥ ያለ አንድ ጤነኛ ሰው ይምረጡ።

 • እንክብካቤ ሲሰጡ የፊት መሸፈኛ ያድርጉ።

 • ከተቻለ፣ አብረውት የሚኖሩትን ለመጠበቅ፣ የታመመውም ሰው የፊት መሸፈኛ ማድረግ አለበት።