እርዳታ ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

211infoእርስዎ ወይም ቤተሰብዎ የቤት ኪራይ ባለመክፈልዎ ለቀው እንዲወጡ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ ከተቀበሉ፡ ቤት ለቀው እንዳይወጡ ከለላ ለማግኘት የሚረዳዎት የቤት ኪራይ እርዳታ ፈጣን-ክፍያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት ወዲያውኑ 2-1-1 ይደውሉ።

የኦሪገን የድንገተኛ አደጋ ኪራይ ድጋፍ ፕሮግራም (Allita):  ከረቡዕ፣ ኖቨምበር 1፣ ከሌልቱ 11፡59 ሰዓት ጀምሮ.፣ የኦሪገን የአጣዳፊ ጊዜ ኪራይ እርዳታ ፕሮግራም አዳዲስ ማመልከቻዎች መቀበሉን ለአፍታ ያቆማል። ይህ ለአፍታ ማቆም ቢያንስ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን አስቀድመው ያጠናቀቁ እና ማመልከቻ ያስገቡ ሰዎችን አይነካም። በአፕሪል 2020 እና ጁን 2021 መካከል የተጠራቀመ የአሁን የቤት ኪራይ ወይም ያለፉ የቤት ኪራይ ለመክፈል እርዳታ ከፈለጉ፣ ላፍታ ማቆም ከመጀመሩ በፊት ለዚህ ፕሮግራም ያመልክቱ። ማመልከቻውን ለመሙላት እርዳታ ከፈለጉ ለእርዳታ 2-1-1 ይደውሉ።

ከቤት ስለ ማስወጣት ጥበቃ መረጃ

የኦሪገን በግዛት አቀፍ ደረጃ የወጣ ከቤት የማስወጣት እገዳ ከሰኔ 30፡ 2021 ዓ.ም ጀምሮ ጊዜው ያለፈበት ሲሆን ከእንግዲህ በኋላ አይሰራም።

ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ የኦሪገን ተከራዮች የቤት ኪራይ እርዳታ አገልግሎት ለማግኘት ካመለከቱ እና የማመልከቻ ሰነዳቸውን ለአከራዮቻቸው ካሳዩ በ የኦሪገን ምክር ቤት ሕግ 278 መሰረት ኪራይ ስላልከፈሉ እንዳይባረሩ ከለላ ያገኛሉ። በ Multnomah County ውስጥ የሚኖሩ ብቁ ተከራዮች አስፈላጊውን ማሳሰቢያ ለአከራዮቻቸው አስፈላጊውን ካሳዩ በኋላ የ 90 ቀናት ከለላ ወይም ጥበቃ የማግኘት መብት ሊኖራቸው ይችላል። ይህ የ 90 ቀናት የሚጀምረው ተከራዩ የኪራይ ድጋፍ ማመልከቻውን ሰነድ ለአከራዮቻቸው ከሚያቀርቡበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ተከራዮች ማመልከቻውን ካስገቡበት የኪራይ እርዳታ አቅራቢ ተገቢውን ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

ይህንን አጥብቀን የምንመክርበት ምክንያት እንደሚከተለው ነው፦ ተከራዮች የቤት ኪራይ መክፈል ካልቻሉ ወዲያውኑ ለኪራይ እርዳታ ማመልከት አለባቸው።

የማመልከቻዎን ማስረጃ እንዴት እና መቼ ማስገባት እንዳለብዎ በተመለከተ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉዎት፡ እባክዎን የኪራይ ድጋፍ አቅራቢዎን፣ ወይም የኦሪገን የሕግ ማእከልንየተከራዮችን ማኅበረሰብ ጥምረት፣ ወይም የኦሪገን የሕግ ድጋፍ አገልግሎቶችን ያነጋግሩ።

ከአፕሪል 2020 እስከ ጁን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ ተከራዮች በቤት ኪራይ ዕዳ ምክንያት ሊባረሩ እንደማይችሉ እና ያንን ኪራይ መልሰው ለመክፈል እስከ ፈብሯሪ 28 ቀን 2022 ዓ.ም ድረስ ጊዜ እንደሚሰጣቸው እባክዎ ይወቁ።

እርስዎ ወይም ቤተሰብዎ የቤት ኪራይ ባለመክፈል ከቤት እንዲወጡ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ ከተቀበሉ፡ ወዲያውኑ 2-1-1 ይደውሉ።

በ Multnomah ካውንቲ የኪራይ ድጋፍ ለመቀበል ብቁ መሆን

Happy black family hugging and embracing on couchየ Multnomah ካውንቲ ነዋሪ ከሆኑ እና በበሽታው ወረርሽኝ ምክንያት የቤት ኪራይዎን (የአሁኑ እና ጊዜው ያለፈበት) ለመክፈል እየታገሉ ከሆነ፡ እርዳታ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ብቁ ለመሆን ቀጥሉ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ ማሟላት አለብዎት

  1. በኦሪገን ውስጥ የሚኖር ተከራይ ሆነው ያልተከፈለ የኪራይ እዳ ያለብዎት።
  2. አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤተሰብዎ አባላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሽታ የቤት ኪራይ ወይም መገልገያዎችን የመክፈል አቅማቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዴት እንደጎዳ ማሳየት ይችላሉ።
  3. የእርስዎ ዓመታዊ የቤተሰብ ገቢ ከቤተሰብዎ መጠን ከአከባቢው መካከለኛ ገቢ 80% ወይም ከዚያ በታች ነው።  የገቢዎን ብቁነት ለመወሰን ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ ይጠቀሙ።

የቤተሰብ ብዛት 

80% አካባቢ መካከለኛ ገቢ (AMI) 

1 $54,150
2 $61,900
3 $69,650
4 $77,350
5 $83,550
6 $89,750
7 $95,950
8 $102,150